የ Seattle Metro Chamber of Commerce and Public Health (ሲያትል ሜትሮ ንግድ እና የህዝብ ጤና ምክር ቤት) - የ Seattle እና King County ካውንቲ ንግዶችን፣ ሰራተኞችን እና ደንበኞችን የክትባት ማረጋገጫውን ስኬታማ ስላደረጉ ያመሰግናሉ።

በህብረተሰብ አቀፍ ጥረት በ King County የ COVID-19 ስርጭትን ለመቀነስ፣ የክትባት ማረጋገጫ መስፈርቱን ማለፍ የምንጀምርበት አዲስ የወረርሽኙ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል።

 

የክትባት ማረጋገጫን ለማቆም ለምን ወደፊት እንሄዳለን።

እንደ ማህበረሰብ እርስ በርስ እንድንጠባበቅ ወደፊት የምንሄድበትን መንገድ እንዳገኘን ሳይንሳዊ ትንተና እና ውሂብ ያሳያል።

  • ተጨማሪ ሰዎች አሁን ክትባት ወስደዋል እና ከከባድ COVID-19 ተጠብቀዋል። የ King County የክትባት ማረጋገጫ መስፈርት ተቀባይነት ያገኘ በመሆኑ፣ ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች ቁጥር ከጠቅላላው ህዝብ 68% የነበረው አሁን ወደ 80% ገደማ አድጓል። ከእነዚያ ውስጥ 12 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ 87% የሚሆኑት ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሲሆኑ 95% የሚሆኑት የክትባቱን ተከታታይ ጀምረዋል።

  • የ Public Health – Seattle & King County (ህዝብ ጤና - ሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ) አሁን ያለው የኢንፌክሽን መጠን በፍጥነት እያሽቆለቆለ ነው፣ የሆስፒታል የመተኛት ቁጥር እየተሻሻለ እና ሆስፒታሎች ለታካሚ ብዛት በተሻለ ሁኔታ መንከባከብ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

ተያያዥ

የ COVID-19 ክትባትን ይውሰዱ

በ King County ውስጥ የሚኖሩ፣ የሚሰሩ ወይም የሚማሩ ከሆነ፣ የ COVID-19 ክትባት ለማግኘት ቀጠሮ ለማስያዝ ይመዝገቡ ወይም ብቅ ይበሉ።

ስለ COVID-19 ክትባት ሁኔታዎ ማረጋገጫ ያግኙ

የ Centers for Disease Control & Prevention (CDC፣ የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል)  የክትባት ካርድዎን በአስተማማኝ ቦታ ያስቀምጡ። ካርድዎ ከጠፋብዎ፣ አማራጮችዎን ይመልከቱ።

ጥያቄዎች?

ለማናቸውም ፈጣን ጥያቄዎች King CountyPublic Health ን ያነጋግሩ

coronavirus@kingcounty.gov

የ KING COUNTY ን ደህንነት ይጠብቁ!

 

  • ወረርሽኙን የመቀነስ ግቦቻችንን ለማሳካት እና ለማቆየት ንግዶች አሁንም እስከ ማርች 1 የክትባት ማረጋገጫ ይጠይቃሉ።

    ለበለጠ መረጃ እና ለንግድዎ የዚህን መመሪያ መደምደሚያ ለማሰስ እዚህ ጠቅ ያድርጉ