Gym Workout

የ King County የክትባት ማረጋገጫ ደንብ ማርች 1 ያበቃል

ለንግድዎ ይህ ምን ማለት ነው...

 

ወደሚከተሉት ለመግባት ከአሁን በኋላ የክትባት ማረጋገጫ አያስፈልግም፡-​

የቤት ውስጥ ምግብ ቤቶች እና ባሮች

ተያያዥ

የ COVID-19 ክትባትን ይውሰዱ

በ King County ውስጥ የሚኖሩ፣ የሚሰሩ ወይም የሚማሩ ከሆነ፣ የ COVID-19 ክትባት ለማግኘት ቀጠሮ ለማስያዝ ይመዝገቡ ወይም ብቅ ይበሉ።

 

ስለ COVID-19 ክትባት ሁኔታዎ ማረጋገጫ ያግኙ

የ Centers for Disease Control & Prevention (CDC፣ የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል)  የክትባት ካርድዎን በአስተማማኝ ቦታ ያስቀምጡ። ካርድዎ ከጠፋብዎ፣ አማራጮችዎን ይመልከቱ።

በሥነ ጥበብ እና በመዝናኛ ቦታዎች

ጂሞች

ከ 500 ሰዎች በላይ ያሉባቸው የውጪ ዝግጅቶች

የስፖርት ዝግጅቶችን፣ ኮንሰርቶችን እና ትርኢቶችን ጨምሮ

እንደ ሠርግ እና ድግስ ላሉ የግል ስብሰባዎች የቤት ውስጥ ዝግጅት የተከራዩ ቦታዎች

ንግዶች አሁንም የክትባት ማረጋገጫ ሊጠይቁ ይችላሉ እና የሕዝብ ጤና ባለሥልጣናት ማናቸውንም ለውጦች እስካላሳወቁ ድረስ የ King County ጭምብል የማድረግ ትእዛዝን መተግበር መቀጠል አለባቸው

ወረርሽኙን የመቀነስ ግቦቻችንን ለማሳካት እና ለማቆየት ንግዶች አሁንም እስከ ማርች 1 የክትባት ማረጋገጫ ይጠይቃሉ።

አዲስ! ለንግድዎ የክትባት ማረጋገጫ ምልክት የራስዎን ሎጎ ያክሉ።

እነዚህን ምልክቶች በ 'Word' ያውርዱ፣ ከዚያም ከታች በተመለከተው ቦታ ላይ የራስዎን ሎጎ ያክሉ።

 

ከማርች 1 በኋላ፣ ከንግዶች የሚጠየቀው ይሄ ነው፦

ሠራተኞችን እና ደንበኞችን ጭምብል ማስደረግ

የክትባት ማስረጃ ወይም አሉታዊ የምርመራ ውጤት ማሳየት

የክትባት ማረጋገጫ ምልክቶችን ማሳየት

  • የ King County ውሂብ በ COVID-19 ላይ ነገሮችን እንደቀለበስን፣ እና አሁን ይህንን መስፈርት ለማንሳት ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ ያሳያል። የህብረተሰብ ጤና ወደዚህ ውሳኔ የመጣው ወደ ወረርሽኙ አዲስ ምዕራፍ እየገባን ስለሆነ ነው።

  • ወረርሽኙን የመቀነስ ግቦችን ለማስቀጠል፣ መስፈርቱ ማርች 1 እስኪያልቅ ድረስ ሰራተኞች የክትባት ሁኔታን ማረጋገጥ መቀጠል አለባቸው። የዚህ መስፈርት ማብቂያ ጋር ደርሰን ማቆም አንችልም።

  • ይህ መስፈርት እያለቀ ሳለ፣ የ  King County ጭንብል መስፈርት ከ Public Health (ህዝባዊ ጤና) ባለስልጣናት ተጨማሪ ዝማኔዎች እስኪደርሱ ድረስ ተግባራዊ ይሆናል።

የክትባት ካርዶችን መመልከት ለመቀጠል ተቀባይነት አለዎት። ከዚህ በታች በካውንቲው የማይፈለግ መሆኑን በማንፀባረቅ አሁንም የክትባት ማረጋገጫ እንደሚፈልጉ ለደንበኞች ለማሳወቅ በንግድዎ ውስጥ ማሳየት የሚችሉት የተሻሻለ ምልክት አለ።

ከማርች 1 በኋላ የክትባት ማረጋገጫ የሚጠይቅ ምልክት ያውርዱ

 

 

የክትባቱን ማረጋገጫ መስፈርቱን እየጠበቁ ከሆነ ለደንበኞች መንገር የሚችሉት የሚከተለው ነው፡-​

  • የእኛ ንግድ በአሁኑ ጊዜ የክትባት ማረጋገጫ ወይም አሉታዊ የምርመራ ውጤትን ይፈልጋል። የእርስዎን ግንዛቤ እናደንቃለን።

  • የእርስዎ ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው! ምንም እንኳን ካውንቲው የክትባት ማረጋገጫ ስልጣኑን ለማንሳት ቢወስንም COVID-19 አሁንም ለብዙ ማህበረሰባችን ስጋት ስለሆነ ሂደቱን ለማስቀጠል ወስነናል።